ሁሉም ተቋራጭ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ተባለ

Published by corporate communication on

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሊት በታቀደው መሰረት እንዲከናወን ሁሉም ተቋራጮች ተናበው እንዲሰሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አብርሃም በላይ አሳሰቡ።

ዶ/ር አብርሃም የግድቡን ሥራዎች ከተመለከቱ በኋላ ከተቋራጮች ጋር ሲወያዩ እንደተናገሩት ተናቦ በመስራት የታሰበውን ውጤት ለማምጣት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል።

በመሆኑም የቅድመ ኃይል ማመጨት ሥራውንና የሁለተኛ  ዙር የውሃ ሙሌቱን በዕቅዱ መሰረት ለማጠናቀቅ  ሁሉም ተቋራጭ የተሰጠውን ኃላፊነት  በአግባቡ መወጣት አለበት ብለዋል።

ተቋራጮቹ ዓመቱን ሙሉ 24 ሰዓት በመስራትና በመናበብ እንዲሁም ግብዐታቸውን በማቀናጀት በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲፈፅሙ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ዶ/ር አብርሃም  አረገግጠዋል።

ተቋራጮቹም የሚሰሯቸውን ስራዎችና የጊዜ ሰሌዳቸውን በማቅረብ ውይይት ተካሂዶበት ግብረመልስ ተሰጥቷቸዋል።

በየወሩ በመገናኘት አፈፃፀሞችን ለመገምገም ቀጠሮ  ይዘዋል።

Categories: ዜና

0 Comments

Leave a Reply

Avatar placeholder

Your email address will not be published.

2 × three =