የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ

በኢትዮጵያ የመብራት ታሪክ የሚጀምረው በ1880ዎቹ መገባደጃ ላይ ነው። በዳግማዊ አጼ- ሚኒሊክ የጀመረው አገልግሎት በአንድ የናፍታ ጄኔሬተር የብሔራዊ ቤተ መንግስትን በማብራት ነው። የናፍታ ጀነሬተሩ ከጀርመን መንግስት የተገኘ ስጦታ ነበር።

የ ኢኤኃ ታሪክ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመሰራረት

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ መብራት ኃይል ባለሥልጣን (በቀድሞ የእንግሊዝኛ ምዕፃሩ EELPA) በ1948 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን የአወቃቀር ማሻሻያ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን (EEPCo) የሚል ስያሜ ያዘ፡፡ ኮርፖሬሽኑ በ2006 ዓ.ም. እንደገና ወደ ሁለት ተቋማት ተከፍሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) በሚል እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 302/2006 እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 381/2008 መሠረት የሚያከናውናቸው ዝርዝር ተግባራት በዝርዝር ተደንግገዋል፡፡ በመሆኑም ተቋሙ በተሻሻለው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 381/2008 መሰረት የተቋቋመባቸው ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የኤሌክትሪክ አቅርቦት ሥርዓት

በአሁኑ ጊዜ በኃይል መሰረተ ልማት የተገናኙት ማመንጫዎች (ICS) 22 ሲሆኑ በዋነኝነት የውሃ ኃይል ማመንጫ እና የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪም ተቋሙ ከደረቅ ቆሻሻ እና ከከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይል የሚያመነጩ ጣቢያዎችም አሉት፡፡

ግብረ መልስ

አስተያየት
Scroll to Top