የ ስራ አመራር ቦርድ አባላት

የተከበሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) -( የትምህርት ዝግጅት ሦስተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በአሁኑ ወቅት የኢፌዲሪ የመከላከያ ሚንስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጄንሲ የሳይበር ቴክኖሎጅ ኢንጅነሪንግ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በሙያቸው ኤሌክትሪካል ኢንጂነር ሲሆኑ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

Statement from the Board Chairman

Ethiopians have honored the vision, dreams, hopes, aspirations and sacrifices of their forefathers and mothers with their blood, sweat, tears and prayers! We will prove it again and again that we are the son and daughters of our forefathers and mothers in all fronts, most notably on the power sector which is the enabler to a meaningful development. GERD is our gateway to our prosperity providing energy security along with the future projects in the pipeline.

የተከበሩ አምባሳደር ግርማ ብሩ - ( የትምህርት ዝግጅት በቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የነበሩ፤ የኢኮኖሚ ልማት እና ትብብር ሚኒስትር እንዲሁም ለአምስት ዓመታት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ናቸው። በሙያቸው ኢኮኖሚስት ሲሆኑ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የተከበሩ አይሻ መሀመድ - ( የትምህርት ዝግጅት በቢዝነስ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስትር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ናቸው፡፡ በሙያቸው ሲቪል መሐንዲስ ሲሆኑ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የተከበሩ ኢዮብ ተካልኝ( ዶ/ር) - ( የትምህርት ዝግጅት ሦስተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የሰሩ፤ በታዋቂ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት ሀገሪቱን በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገሪቱን አገልግለዋል በሙያቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሲሆኑ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ - ( የትምህርት ዝግጅት ሁለተኛ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ እና ዋና ኢኮኖሚስት ናቸው፡፡ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በተለያዩ የፋይናንስ ዘርፎች በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል፡፡ በሙያቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሲሆኑ ለሁለት አስርት ዓመታት ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

አቶ አሻብር ባልቻ

ዋና ሥራ አስፈፃሚ

ወ/ሮ ማህሌት ንጉስ - ( የትምህርት ዝግጅት የመጀመሪያ ዲግሪ )

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ወቅት የማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም ባለሙያ፣ የሰኩሪቲ ሞኒተሪንግ እና ምላሽ ኤክስፐርት እንዲሁም የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካይ ናቸው፡፡ በሚያቸው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ሲሆኑ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋማቸውንና ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

አቶ ተሾመ በላይ - (የትምህርት ዝግጅት በአርት ሁለተኛ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ አባል በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ እና የመሰረታዊ ሠራተኛ ማህበር ተወካይ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል የግብርና ልማት ባለሙያ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከፍተኛ ሪፖርተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በሙያቸው የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ሲሆኑ በተለያየ ዘርፍ ሁለት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሀገራቸውን አገልግለዋል።

ወ/ሮ ወይንሸት አበበ - (የትምህርት ዝግጅት በአርት የመጀመሪያ ዲግሪ)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ፀሐፊ ቀደም ሲል በደቡብ አዲስ አበባ እና በዋና መ/ቤት የገበያና ሽያጭ ክትትል ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የአስተዳደር ረዳት በመሆን አገልግለዋል፡፡ በሙያቸው የማርኬቲንግ ባለሙያ ሲሆኑ በተቋሙ ውስጥ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ አገልግለዋል።

ግብረ መልስ

አስተያየት
Scroll to Top